ፑቲን በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እንዲረግብ ሁሉንም የተቻላቸው ጥረቶች እያደረጉ መሆኑን ክሬምሊን አስታወቀ

በክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በተሰጡ መግለጫዎች፦ ፑቲን ለባሕረ ሰላጤው የአረብ አገራት አቻዎቻቸው፣ በመሠረተ ልማቶቻቸው ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በተመለከተ ያላቸውን ጥልቅ ስጋት ለኢራን እንደሚያደርሱ ቃል ገብተዋል።

ሩሲያ የሌሎች ሀገራትን ሉዓላዊነት ታከብራለች፤ በጉዳዮቻቸው ላይም ጣልቃ አትገባም፤ ሌላ ማንኛውም አቋም ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር የሚቃረን ይሆናል

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በተባባሰው የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የሲቪሎችን ጉዳት የሚያስከትሉ ውጊያዎችን ማቆም አፈላጊ ነው ነው ብለዋል፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እያመረተች ስለመሆኑ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ብለዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ፣ በኢራን ዙሪያ ያለው ውጥረት በአስቸኳይ እንዲረግብ፣ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ወደ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሂደቶች እንዲመለሱ ሩሲያ ጥሪ አቅርባለች።

የውጪ ጉዳይ መስሪቤቱ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረግ የባህር ላይ ትራንስፖርት መቋረጥ የዓለምን የነዳጅ እና የጋዝ ገበያ የማናጋት አደጋ እንዳለው ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።

የካቲት 24/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *