ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ወራት ከቡና የወጪ ንግድ 1.47 ቢሊዮን ዶላር አገኘች – ግብርና ሚኒስቴር

በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 600 ሺህ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ በማቅረብ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን ባለፉት ሰባት ወራት 217 ሺህ ቶን ቡና ማቅረብ ተችሏል።

የግብርና ሚኒስቴር በቡና ግብይት እሴት ሰንሰለት ውስጥ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እና መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ከቡና ላኪዎች እና አቅራቢዎች ጋር አካሂዷል።

ውይይቱ ዘመናዊ የቡና ግብይት ስርዓት በመዘርጋት በዓለም ገበያ የኢትዮጵያን የቡና አቅርቦት ውጤታማነትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የካቲት 24/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *