የኬንያ መንግስት በባለፈዉ ወር እንደገለፀዉ ከ 1 ሺህ በላይ ኬንያዉያን ለሩሲያ ለመዋጋት መመልመላቸዉን ተናግሮ ነበር።
አሁንም በዚህ ጦርነት 89 ኬንያዉያን በጦርነቱ እየተፋለሙ ይገኛሉ ተብሏል።
በትናንትናው እለት በናይሮቢ ጎዳናዎች የወጣቶቹ ቤተሰቦች ” ልጆቻችን ይመለሱ” የሚል መፈክሮች በመያዝ ወጥተዋል።
ለጦርነቱ የተመለመሉ ኬንያዉያን ወጣቶች ፎቶ በጎዳናዎቹ ላይ ይዘዉ የታዩት የወጣቶቹ ቤተሰቦች መንግስት እንዲረዳቸዉ ጠይቀዋል ተብሏል።
አፍሪካ ኒዉስ ያነጋገራቸዉ በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የቮካል አፍሪካ ኦፊሰር የሆኑት ኦዲያምቦ ኦጂሮ የኬንያ መንግስት በዚህ የምልመላ ጉዳይ ይሳተፋል ሲሉ ገልጸዋል።
የዜና ወኪሉ ዘገባ በዚህ የጦርነት ምልመላ የሩሲያ እና የኬንያ መንግስት ባለስልጣናት ከኤጀንሲዎች ጋር በመመሳጠር ኬንያዊያን ወጣቶችን ለጦር ግንባር ማሳተፋቸዉን ፅፏል።
የወጣቶቹ ቤተሰቦች ሩሲያ ዉስጥ ያሉ ኬንያዉያን ሞተዉም ከሆነ በህይወትም ካሉ ወደ ሀገራቸዉ ይመለሱልን ሲሉ አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
መንግስት በዩክሬን በጦር እስር ላይ የሚገኙ ኬንያዉያን ወደ ሀገራቸዉ ለመመለስ እየሰራ ነዉ የሚሉት የኬንያ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል።
በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት 39 ኬንያዉያን ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን 28ቱ ደግሞ ያሉበት የማይታወቅ መሆኑን አፍሪካ ኒዉስ ዘግቧል።
ከህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር እና የግዳጅ ምልመላ ጋር የተያያዘዉ ጉዳዩ እስካሁን ሁለት ኬንያዉያን በህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር ክስ ተመስርቶባቸው እንደሚገኝ ዘገባዉ ጠቅሷል።
ቁምነገር አየለ
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
