የግዛቱ ምክትል አስተዳዳሪ ጃሊል ሃሳኒ፥በቅርቡ የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃቶች በሺራዝ ከተማ ላይ 20 ሰዎች ሲሞቱ 30 ቆስለዋል ብለዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በከተማይቱ ዚባሻህር አካባቢ በሚገኝ የመኖሪያ ክፍል ውስጥ ነዉ ተብሏል።
በጥቃቱም ንጹሃን ዜጎችን ተገድለዋል ሲል የኢራን የመንግስት ሚዲያ ዘግቧል።
ከዚህ ቀደም በሽራዝ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት የህክምና ባለሙያዎች መገደላቸውን መዘገቡን አልጀዚራ አስታውሷል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
