ሁለቱ አገሮች በድንበሮቻቸው ላይ በገቡበት ውዝግብ በጋልዋን ሰምጠ ሸለቆ አካባቢ 20 የህንድ ወታደሮች መገደላቸው የተነገረ ሲሆን ቻይና አደገኛ ጦር መሣሪያ መጠቀሟን የሚያመመለከት መረጃ መውጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡
ቻይና ወታደሮቿ እንዳልሞቱባት ብትገልፅም ሁለቱ አገሮች ግን መወነጃጀላቸውን ቀጥለዋል፡፡
የመከላከያ ጉዳዮች ተንታኙ አጃይ ሹክላ ሲናገሩ ቻይና ይህን አይነቱን መሣሪያ መጠቀሟ ወንጀል እንደሆነና በ1996 በአገራቱ የተፈረመውን ስምምነት የሚጥስ ነው ብለዋል፡፡
የህንድ እና የቻይና ወታደሮች በ4ሺህ 2 መቶ 67 ሜትር ርቀት ላይ ሆነው እንደሚታኮሱም ታውቋል፡፡
ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ህንድ እና ቻይና የድንበር ላይ ውዝግብ ማንሳታቸው የሚታወስ ሲሆን ይህም ቀጠናውን ወደለየለት ጦርነት እንዳያስገባ ስጋትን ጭሯል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በአባቱ መረቀ
