እስራኤል የኢራኑ ከፍተኛ የጸጥታ አማካሪ አሊ ላሪጃኒ በሶሪያ በተሰነዘረ ጥቃት መገደላቸውን አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ኃይል በዛሬው ዕለት በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ በፈጸመው የአየር ጥቃት፣ የኢራኑ ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ የቅርብ አማካሪ የሆኑት አሊ ላሪጃኒ መገደላቸውን ቢቢሲ የእስራኤልን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል።

አሊ ላሪጃኒ ቀደም ሲል የኢራን የፓርላማ አፈ-ጉባኤ እና የኒውክሌር ጉዳይ ዋና ተደራዳሪ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ በኢራን ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካላቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ።

ጥቃቱ የተፈጸመው ላሪጃኒ በደማስቆ ከሶሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ በማድረግ ላይ እያሉ እንደሆነ ተገልጿል።

እስራኤል በሶሪያ ውስጥ በሚገኙ የኢራን ኢላማዎች ላይ የምታደርገውን ጥቃት አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን፣ የላሪጃኒ መገደል በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል።

እስካሁን ድረስ ከኢራን መንግስት በኩል በይፋ የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም፣ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ግን ጥቃቱ መፈጸሙን ዘግበዋል።

ልዑል ወልዴ

መጋቢት 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *