የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለ1447ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል ልዩ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ።

ተቋሙ በበዓላት ወቅት የሚኖረውን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የመስመር ጥገና፣ የምሰሶዎች ለውጥ እና የትራንስፎርመሮችን አቅም የማሳደግ ስራዎችን መስራቱን አስታውቋል።

እንዲሁም በዋዜማው እና በበዓሉ ወቅት የሚያጋጥሙ ድንገተኛ መቆራረጦችን ለመፍታት የተቋቋመው ልዩ የአስቸኳይ ጥገና ግብረ-ኃይል በሁሉም ዘርፎች ተሰማርቶ ይገኛል ተብሏል።

በተጨማሪም የቅድመ-ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች በበዓሉ ዕለት ሊያጋጥም የሚችለውን እንግልት ለመቀነስ የኃይል መጠን መኖሩን አረጋግጠው አስቀድመው እንዲሞሉ አገልግሎቱ አሳስቧል።

ደንበኞች ማንኛውንም መረጃና ጥቆማ በ905 ወይም በ904 የጥሪ ማዕከላት፣ በአገልግሎቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እንዲሁም በአቅራቢያ በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ቢሮዎች ማሳወቅ እንደሚችሉ ተገልጿል ።

ሐመረ ፍሬዉ

መጋቢት 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *