የኢትዮጲያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን በረራ ያደረገበት ታሪካዊ እለት እየተከበረ ነው

የኢትዮጲያ አየር መንገድ መጋቢት 30 1938 ዓ/ም ነበር ከ አ.አ -አስመራ አድርጎ ወደ ካይሮ የመጀመሪያ በረራውን ያደረገው።

የአየር መንገዱ ከፍተኛ ሀላፊዎች አየር መንገዱ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በማስመልከት በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰተዋል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱን 80ኛ ዓመት አስመልክተው ባደረጉት ንግግር በ1938 ዓ/ም ሀ ብሎ የጀመረው የአየር መንገዱ የበራራ ጉዞ በ1960ዎቹ ምእራብ አፍሪካን ከ ምስራቅ አፍሪካ በማገናኘት ጉዞውን ማጠናከሩን ተናግረዋል።

በ1960ዎቹ አፍሪካን ከቻይና ጋር እንዲሁም በ1990 ኒዮርክ ፥ዋሺንግተን በተጨማሪም የአውሮፓ ሀገራት ላይ ተደራሽ ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው በዚህ መልኩ መዳረሻውን በማስፋት በአሁኑ ወቅት ከ 145 በላይ አለም አቀፍ መዳረሻዎች እንዳሉት አብራርተዋል።

በተለይ ከ 1976 ዓ/ም በኃላ አዳዲስ አውሮፕላኖችን በየጊዜው በማስገባት እና እራሱን በማሳደግ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ፣ የአውሮፕላን ጥገና ክፍልንም በማቋቋም የትኛውንም የአውሮፕላን ክፍል በራ ሱ የመጠገን ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡

የኢትዮጲያ አየር መንገድ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን የአቬሽን ግሩፕ እንዲሆን ስለመደረጉ እና ከአፍሪካ ትልቁ የአቬሽን ዮኒቨርስቲ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በደርግ መንግስት፣ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት፣ኮቪድ 19 እና ሌሎችም ከባድ ፈተናዎች እንዳጋጠሙት እና ይህንንም ተቋቁሞ በስኬት ማለፍንም አስታውቀዋል።

በቀጣይ በቢሾፍቱ የሚገነባው አየር መንገድን ማጠናቀቅ፣ የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ የበራራ መዳረሻዎችን ማስፋፋት፣ የጭነት መጠንን በመጨመር ፣ የሰራተኞችን አቅም በማሳደግ እና በሌሎችም ዘርፎች እራሱን እያጎለበት እንደሚጓዝ አቶ መስፍን አስታውቀዋል።

አየር መንገዱ ከአህጉር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ስኬትን እንዲቀዳጅ ያደረጉ ፣በጡራታ የተገለሉ እና በስራ ላይ የሚገኙ ሰራተኞቹ ፣ ደንበኞች እና አጋር ድርጅቶች በዚሁ እለት ተመስግነዋል።

አየር መንገዱ የተመሰረተበትን 80ኛ አመት በሚቀጥሉት ሳምንታት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ እንደሚቀጥልም ታውቋል።

የውል ሰው ገዝሙ

መጋቢት 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *