በኢትዮጵያ የሚካሄደው ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ወጣቱ ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ። ይህ ጥሪ የተላለፈው “የወጣቶች ድምፅ ለሰላማዊ ምርጫ” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው አገራዊ የንቅናቄ መድረክ ላይ ነው።
ወ/ሮ ሙና አህመድ በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የወጣቶች ዘርፍ ሀላፊኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በታሪካዊ የዴሞክራሲ ሽግግር ምዕራፍ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ በዚህ ሂደት ውስጥ የሀገሪቱ ትልቁ የሰው ኃይል የሆነው ወጣት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በምርጫ ሂደቱ ውስጥ የወጣቱ በንቃት መሳተፍ የምርጫውን ተአማኒነት ከማረጋገጥ ባለፈ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የፖሊሲ አውጪዎች ለወጣቱ አጀንዳዎች ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ የሚያስገድድ መሆኑ ተገልጿል።
ባለፈው ስድስተኛ አገራዊ ምርጫ ከ150 ሺህ በላይ ወጣቶች በምርጫ አስፈጻሚነትና በታዛቢነት በመሰማራት ለምርጫው ሰላማዊነትና ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ያስታወሱት የመድረኩ ተሳታፊዎች፣ አሁንም ወጣቱ ያንን ልምድ በመጠቀም ለሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ስኬት መትጋት እንዳለበት አሳስበዋል።
በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው፣ የፖለቲካተሳትፎ ማለት የምርጫ ካርድ መውሰድና ድምፅ መስጠት ብቻ ሳይሆን፣ የፓርቲዎችን ማኒፌስቶ በጥልቀት መመርመርና ለወጣቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ለኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ቅድሚያ የሚሰጡ አማራጮችን መለየት ጭምር ነው።
ወጣቱ በምክንያትና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ በማድረግ የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያሸጋግርም ጥሪ ቀርቧልል።
ለዓለም አሰፋ
መጋቢት 30/2018 ዓ.ም
