የባህር ላይ ወንጀሎች መስፋፋትን ጨምሮ ለጂኦ ፓለቲካዊ ዉጥረቶች በቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ ሰላጤ ቀጠናን እየፈተነ ስለመገኙቱ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ባሰናዳዉ በባህር ላይ አስተዳደር ዙሪያ ያተኮረ ኮንፈረንስ ላይ እንደተገለፀዉ የአለም የፀጥታ ችግሮች የንግድ እና የሀይል መተላለፊያ መስመሮችን እያስተጓጎሉ መሆኑን ተከትሎ ጫናዉ መበርታቱ ተነስቷል።
የዉጪ ጉዳይ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጃፋር በድሩ ቀይ ባህር አካባቢ ያሉ ጥቃቶች ሀገራትን ለተጨማሪ ወጪ መዳረጉን ተናግረዋል።
የመርከቦች ድርጅቶች አቅጣጫ እንዲቀይሩ መገደድ ደግሞ ለሚያደርጉት እያንዳንዱ ጉዞ የ14 ቀናት መዘግየትን የሚፈጥር ስለመሆኑ ያስረዳሉ።
አካታችነት ያለዉ የጋራ ጥቅምን መሠረት ያደረገ የባህር ላይ አስተዳደር ወሳኝ መሆኑ የተነገረበት የዉይይት ኮንፈረንሱ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ ሽብርተኝነትን እና የባሕር ላይ ዝርፊያን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑም የተነገረበት ነበር።
በቀይ ባህር ያለው የጸጥታ ቀውስ በአመት በአማካኝ 12.5 ሚሊዮን ቶን የኢትዮጵያ ጭነት የሚጓጓዝበት የጅቡቲ ወደብ አጠቃቀም ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ስለመሆኑ ይነገራል።
በየአመቱ ከዓለም አቀፍ ንግድ 12 በመቶውን ያህሉን የሚሸፍኑ ጭነቶች የሚጓጓዙበት የቀይ ባህር መስመር አካታች አስተዳደር ሊኖረዉ ይገባል ተብሏል።
ቁምነገር አየለ
መጋቢት 30/2018 ዓ.ም
