የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የትንሣኤ በአልን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን በዛሬዉ ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።
ለበአሉ እስከ 4 ሺህ የእርድ እንስሳት የሚጠበቁ መሆኑን የገለፀዉ ድርጅቱ፤ ለእርድ አገልግሎት በቂ ዝግጅት አድርጊያለሁ ብሏል።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙሉነህ ደሳለኝ፤ ተቋሙ ያለዉ የእርድ ክፍል አነስተኛ መሆን የእርድ እንስሳት ቁጥር ይወስናል በሚል የሚወቀስ መሆኑን አንስተዋል።
ድርጅቱ የእርድ ክፍልን የማስፋት ስራ መስራቱን ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደመ ከ200 እስከ 300 እንስሳት የእርድ አገልግሎት የሚሰጥበትን እስከ 800 በሬ በአንድ ሰአት ዉስጥ አገልግሎት የሚሰጥ ማድረግ መቻሉን ስራ አስፈጻሚዉ ተናግረዋል።
በአሁኑ የበአል ዝግጅት 10 ተጨማሪ መኪናዎችን ለስጋ ማጓጓዣ እንዳዘጋጀ የተናገረዉ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት፤ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ የተቋሙን የሎጎ እና ብራንዲንግ ለዉጥም ይፋ አድርጓል።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ቅርጫን በዲጂታል ቅርጫ እንዲካሄድ ለማድረግ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙም ተገልጿል።
ለህብረተሰቡ የእርድ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሞባይል ተንቀሳቃሽ የቄራ አገልግሎት ለመስጠት ጥናት እየተደረገ ነዉ ተብሏል።
መጪዉን የትንሣኤ በአል የስጋ ተደራሽነት አስመልክቶ ያለዉን የነዳጅ እጥረት እክል እንዳይፈጥር ከነዳጅ ድርጅት እና ንግድ ቢሮ ጋር በተደረገ ዉይይት መኪኖቹ ነዳጅ እንዲያገኙ ስለመደረጉም ተነስቷል፡፡
የአዲስ አበባ አርሶአደሮች እና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ፀጋ ለማ፤በሶስቱም የአዲስ አበባ ቄራዎች ከ40 በላይ የስጋ ምርመራ ባለሙያዎች እንዳሉ ገልፀዋል።
የህገወጥ እርድ መቀነስ ከሸገር እና አዲስ አበባ ቄራዎች ጋር በትብብር ለመቆጣጠር የሚያስችል ስራ ዝግጁ መሆኑም ተነግሯል።
ዶ/ር ፀጋ በሶስቱም የአዲስ አበባ ቄራዎች ከ40 በላይ ባለሙያዎችን እንዳላቸዉ ገልፀዋል።
በባለፉት ዘጠኝ ወራት 71 የሚጠጉ እንስሳት በሽታ የተገኘባቸዉ እንዲሁም ከ200 በላይ እንስሳት ብቁ ባለመሆናቸዉ የተመለሱ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።
የተሽከርካሪ ስታንዳርድ እየተጠበቀ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ፍቃድ እየተሰጠ እንደሚገኝ ዶ/ር ፀጋ ገልፀዋል።
በቄራ ድርጅት ያልታረደ ስጋ የተገኘባቸዉ 1 ሺህ 79 ልኳንዳ ቤቶች መገኘታቸዉም ተነግሯል።
ቁምነገር አየለ
መጋቢት 30/2018 ዓ.ም
