የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ባዘጋጀውና ኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብ/ቡድኗን ባሳተፈችበት የወዳጅነት ጨዋታ ድል ቀንቷታል።
በቱርክ መዲና ኢስታንቡል እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ዛሬ ከኡራጓይ ጋር አድርጋለች። በውጤቱም 3-0 አሸንፋለች። ሁሉንም የአሸናፊነት ጎሎች ከመረብ በማሳረፍ ሀትሪክ የሰራችው ደግሞ ህድአት ካሱ ናት።
ምስጋናው ታደሰ
መጋቢት 30/2018 ዓ.ም
