በአውሮፓና እስያ ከፍተኛ እውቅና ያለው ዋይልድቤሪስ ለኢትዮጵያ የንግድ ማህበረስብ የኢ ኮሜርስ የንግድ ስርዓቱን አሰጀመረ። ይህም ሸማቾች ከአትዮጵያ በቀጥታ እንደ ቡና፣ ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ መገልገያዎች ፣ የቤት እቃዎች እና የተፈጥሮ መዋቢያዎች ያሉ ታዋቂ ምርቶችን በቀጥታ እንዲሸምቱ ያስችላቸዋል ።
ኢትዮጵያ የዋይልድቤሪስ አስራር ከተዘረጋባቸው ሀገራት ውስጥ 11ኛዋ ያደርጋታል። በዚህ የመጀመሪያው ምዕራፍ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን ለሩሲያ ደንበኞች እንዲያቅርብ ይስችላቸዋል ፣ በቀጣይን ምዕራፍ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ምርቶችን ለኢትዮጵያ ሸማቾች በማምጣት የንግድን ዘርፉን የማሳደግ እቅድ አለ።
ዋይልድቤሪስ ከኢትዮጵያ ወደ ሩሲያ ወይንም ከሩሲያ ወደ ኢትዮጵያ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ ከኢትዮጵያ ፖስታ ጋር ስምምነት ፈፅሞል ።
“ በኢትዮጵያ የኢ-ኮሜርስ እድገት ትልቅ አቅም እንዳለው የሚያሳይ ጥሩ ምልክቶችን አይተናል ፤ ። ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በፍጥነት እያደገች ያለች ሀገር መሆኗ ፣ እምቅ የወጣት ህይልና ዲጂታል ተጠቃሚ ህዝብ ያላት መሆኗ እና እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት ዲጂታል 2030 በማስፋፋት ዲጂታላይዜሽን የኢ-ኮሜርስ ስርዓቶች ለመዘርጋት ያለው ቁርጠኝነት ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።
እንደ ቡና ያሉ የኢትዮጵያ ምርቶች ከወዲሁ የበርካታ ደንበኞቻችንን ቀዳሚ ምርጫ ነው፣ በዚህ የኢ-ኮሜርስ ንግድ ሰርዓት አማካኝነት በርካታ የአትየጵያ የንግድ ማህበረሰብ ምርቶች ጠንካራ ፍላጎት የማሳደር አቅም እንዳላቸው እርግጠኛ ነኝ ሲሉ Tatyana Kim, የዋይልድቤሪስ መስራች ተናግረዋል ።
ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በኢ-ኮሜርስ ግንባር ቀደም በመሆን የሰራው ዋይልድቤሪስ በኢትዮጵያ የኦንላይ ንግድን ለማሳደግ ቁልፍ አጋር ለመሆን ተዘጋጅቷል። ለነጋዴዎች የቴክኖሎጂ እውቀት፣ የተሻሻለ የሎጂስቲክስ መስመሮችን ፣ እንዲሁም አዳዲስ ነጋዴዎች ንግዳቸውን በፍጥነት በዋይልድቤሪስ ላይ እንዲጀምሩና እንዲያሳድጉ የሚረዱ አብሮ የተሰሩ የማስታወቂያ እና የድጋፍ አገልግሎቶችን ያቀርባል።
በተጨማሪም ዋይልድቤሪስ የላቁ የፊንቴክ መፍትሄዎችን ለኢ-ኮሜርስ ዘርፍ እንደሚያቀርብ እና ለደንበኞችም ሆነ ለሻጮች የአገልግሎት ልምድን ለማሳደግ ፈጠራዎቹን ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። ነጋዴዎች የዋይልድቤሪስን ምቹ የሎጂስቲክስ ፣ በኤአይ (በሰው ሰራሽ አስተውሎ) የሚሰሩ ትንተናዎችና ማስታወቂያዎችን ተጠቅመው የምርቶቻቸውን ገጾችንና ምስሎችን መፍጠር በቀላሉ ደንበኞቻቸውን መደራስ ያስሽላቸዋል ። ይህም ከከፍተኛ የአሰራር ወጪዎች ይታደጋቸዋል።
የዋይልድቤሪስ የኢ-ኮሜርስ ንግድ ሰርዓት በኢትዮጵያ መጀመር በአፍሪካ ሀገራትና በኢ-ኮሜርስ የንግድ ሰርዓት ገበያው መካከል የዲጂታል ንግድን ለማመቻቸት የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ነጋዴዎችን የደንበኞቻቸውን ቁጥር እንዲያሳድጉና አዳዲስ እድሎችን እንዲከፍቱ ያስችላቸዋል። እ.አ.አ 2025 መጨረሻ አካባቢ ፣ ዋይልድቤሪስ በኢትዮጵያ የኢ-ኮሜርስ እና ተያያዥ መሠረተ ልማቶችን ለማሳደግ ከአፍሪካ ትልቁ የሀብት ፈንድ ከሆነው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር ሽርክና መጀመሩን አስታውቋል።
መጋቢት 30 /2018 ዓ.ም
