የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ አገር ሰራተኞች ስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ ጥብቅ የቁጥጥር መስፈርት አወጣ

ወደ ውጭ አገር ለስራ የሚሄዱ ዜጎች የሚሰጣቸው ስልጠና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዲስ መመሪያ ማውጣቱን አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም በስልጠና ተቋማት ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት ከ100 በላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል።

አዲሱ መስፈርት እያንዳንዱ የስልጠና ክፍል ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ያስገድዳል።

ይህም የንድፈ ሃሳብ መማሪያ፣ የተግባር ልምምድ ክፍል፣ የኬሚካል መያዣ እና የመኝታ ክፍሎችን የሚያካትት ነው።

ስልጠናው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ሲሆን፥እያንዳንዱ ሰልጣኝ ስልጠናውን በአግባቡ መከታተሉን ለማረጋገጥ በክፍሎች ውስጥ የኤ አይ ካሜራዎች ይገጠማሉ ነው የተባለው።

ሰልጣኞች ስልጠናውን አጠናቅቀው ብቁ መሆናቸው ሲረጋገጥም፣ በቀጥታ በሲስተሙ የሚመነጭና በዲጂታል ፊርማ የተረጋገጠ ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

ይህም የምስክር ወረቀት ማጭበርበርን ሙሉ በሙሉ እንደሚያስቀር ተመላክቷል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *