በትራምፕ እና በለንደን መካከል ያለው ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ መያዙ ተነገረ

የብሪታንያው ንጉሥ ቻርልስ በዋሽንግተን እያደረጉት ያለው ይፋዊ ጉብኝት በሁለቱ አገራት መካከል የሻከረውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ቀድሞ ይዞታው የመለሰ ታሪካዊ ክስተት ተደርጎ ተወድሷል።

በዋይት ሃውስ በተዘጋጀው ደማቅ የእራት ግብዣ ላይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባደረጉት ንግግር፥ንጉሡ የኢራንን የኒውክሌር መሣሪያ ታጥቆ የመውጣት ፍላጎት በጥብቅ እንደሚቃወሙ ገልጸዋል።

ትራምፕ በንግግራቸው ‘’ቻርልስ በዚህ ጉዳይ ላይ ከእኔ በላይ ይስማማሉ”በማለት የሁለቱ መሪዎች አቋም የተናበበ መሆኑን ለአለም አሳይተዋል።

ንጉሡ ለኮንግረስ አባላት ባደረጉት ንግግር፤አሜሪካ እና ብሪታንያ “ወደ ውስጥ ብቻ የመመልከት” አዝማሚያን እንዲተዉ እና ለኔቶ እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ጥምረቶች ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።

የቀድሞ የንግሥት ኤልሳቤጥ የኮሙኒኬሽን ጸሐፊ የነበሩት አይልሳ አንደርሰን፥ ንጉሡ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በሆነ መንገድ የአሜሪካን ሕዝብ ልብ ማሸነፍ መቻላቸውን የገለጹ ሲሆን፥ “ንጉሡ በመሪዎች መካከል የነበረውን መቃቃር በማለዘብ ረገድ ‘መርከቧን አረጋግተዋል” ሲሉ  ሌላኛው ባለሙያ ሲሞን ሌዊስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ይህ ጉብኝት በጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በፕሬዝዳንቱ መካከል ለሚኖረው ቀጣይ የሥራ ግንኙነት ምቹ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑ ተመልክቷል።

ሀና ሰይፉ

ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *