ጄምስ ኮሚ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ የግድያ ዛቻ ሰንዝረዋል በሚል ተከሰሱ

የቀድሞው የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚ፥ “86-47” የሚል የቁጥር ምልክት ያለበትን የባህር ዛጎሎች ምስል በኢንስታግራም ገጻቸው ላይ በማጋራታቸው፣ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህይወት ላይ ዛቻ ሰንዝረዋል በሚል በፌዴራል አቃቤ ህግ ተከስሰዋል።

እንደ ክሱ ዝርዝር፥ 86 የሚለው ቁጥር”አንድን አካል ማስወገድ” የሚል የንግግር ዘይቤ ሲሆን፥ 47 ደግሞ 47ኛውን ፕሬዝዳንት ትራምፕን የሚወክል ነው ተብሏል።

ኮሚ የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ በማድረግ ንጹህ መሆናቸውንና ምስሉን ያጋሩት ትርጉሙን ሳያውቁ እንደነበር ገልፀዋል።

የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴል እና ተጠባባቂ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቶድ ብላንች ድርጊቱ የሀገሪቱን ህግ የጣሰ ከባድ ወንጀል ነው ብለዋል።

ኮሚ የቀረበባቸው ሁለት ክሶች እያንዳንዳቸው እስከ 10 ዓመት እስራት ሊያስከትሉ የሚችሉ ሲሆን፥ አሁን ላይ ጉዳዩ በሰሜን ካሮላይና ፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።

ሳራ ዮሐንስ

ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *