የዩክሬን የባህር ኃይል ማዕቀብ የተጣለበትን የሩሲያ የነዳጅ ጫኝ መርከብ በጥቁር ባህር ላይ መምታቱን አስታወቀ።
የዩክሬን ጦር ጠቅላይ መምሪያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ መሰረት፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ከሩሲያዋ የቱዋፕሴ (Tuapse) የባህር ወደብ በስተደቡብ ምስራቅ 210 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ነው።
ለጥቃቱ በባህር ላይ የሚጓዙ ድሮኖች (maritime drones)ጥቅም ላይ መዋላቸውን የጠቅላይ መምሪያው መግለጫ አመልክቷል።
በጥቃቱ በመርከቧ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ሩሲያ ለጦርነት የምትጠቀምባቸውን የኢኮኖሚ ምንጮች ለማዳከም ካለመው እንቅስቃሴ አካል መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ጥቃት ዩክሬን በጥቁር ባህር ላይ ያላትን ወታደራዊ አቅም እያጠናከረች መምጣቷን የሚያሳይ ሌላኛው እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።
ልዑል ወልዴ
ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም
