በደቡባዊ ኮሎምቢያ አንድ ግዙፍ የጭነት መኪና በሰዎች ላይ በመገልበጡ የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ በርካታ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ፤አደጋው የደረሰው እሁድ ዕለት በካውካ ግዛት ደቡባዊ ከተማ በሆነችው ፖፓያን ውስጥ በትርኢት ላይ ያለ መኪና ፍሬን በመበላሸቱ ነው፡፡
የአደጋው ቪዲዮ እንደሚያሳየው ከሆነ፤ መኪናው የጥበቃ አጥር ጥሶ ወደ ሕዝቡ ሲገባና ከኤሌክትሪክ ምሰሶ ጋር ተጋጭቶ ከመቆሙ በፊት ሰዎች ለማምለጥ ሲሮጡ ይታያል።
ባለሥልጣናት በአደጋው እስካሁን ቢያንስ 38 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል።
ኤል እስፔክታዶር የተሰኘው ጋዜጣ የከተማዋን ባለሥልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው አንዲት የ10 ዓመት ሴት ልጅ በቦታው ላይ ሕይወቷ አልፏል።
የፖፓያን ፖሊስ አዛዥ ኮሎኔል ጁሊያን ካስታኔዳ ለኤል ቲየምፖ ለተባለ የዜና ተቋም እንደተናገሩት፤ መኪናው የቴክኒክ ብልሽት እንዳጋጠመው አመልክተዋል።
ሀና ሰይፉ
ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም
