በማሊ በተፈጸሙ ሁለት ጥቃቶች ከ30 በላይ ንጹሃን መገደላቸዉ ተገለጸ

በማዕከላዊ ማሊ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላቸዉ የተባሉ የሽብር ቡድኖች አድርሰዉታል በተባሉ ሁለት ጥቃቶች ከ30 በላይ ንጹሃን መገደላቸዉ ተዘግቧል፡፡

እነዚህ ሁለት ጥቃቶች የተፈጸሙት ጂሃዲስቶች እና ተገንጣይ ቡድኖች በወታደራዊ ጁንታው ይዞታዎች ላይ የተቀናጀ እና መጠነ ሰፊ ጥቃት ካደረሱ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሲሆን፤ይህም በዚች የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ላይ አዲስ የጸጥታ ቀውስ አስከትሏል።

በሳህል ቀጣና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው የጋዜጠኞች ቡድን እንደገለጸው፤ የተገደሉት የመንደሩ ነዋሪዎች ቁጥር ከ50 በላይ ሊሆን እንደሚችልና በርካታ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልጿል።

“መንደሮች ተዘርፈዋል፣ የተወሰኑ ንብረቶችም በእሳት ተቃጥለዋል” ሲል ቡድኑ አክሏል።

“አብዛኞቹ ተጎጂዎች የሚሊሻ አባላት ናቸው፤ ሆኖም ታዳጊዎችና ህፃናትም በጥቃቱ ተገድለዋል” ሲል ምንጩ ለኤኤፍፒ ተናግሯል።

የማሊ ጦር በበኩሉ በሐሙስ ዕለት በአካባቢው “በሽብርተኛ የታጠቁ ቡድኖች ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ” ማካሄዱንና 12 የሚሆኑ ታጣቂዎችን “መደምሰሱን” ገልጿል።

ሰራዊቱ ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *