ቤጂንግ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሺ ጂንፒንግ ጋር ለመገናኘት በዚህ ሳምንት ወደ ቻይና እንደሚያቀኑ አረጋግጣለች።

ከግንቦት 5 እስከ 7 የሚቆየው ይህ ጉብኝት፣ በአስር አመታት ውስጥ አንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ወደ ቻይና የሚያደርጉት የመጀመሪያው ጉዞ ይሆናል ተብሏል፡፡

ይህ ጉዞ በዓለማችን ሁለቱ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች መካከል ያለው ግንኙነት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በሚገኝበት ወቅት የሚደረግ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

እንደ ቦይንግ ፣ ሲቲ ግሩፕ እና ኳልኮም ያሉ የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች ስራ አስፈጻሚዎች ከቻይና ኩባንያዎች ጋር ስምምነቶችን ለማድረግ ከትራምፕ ጋር አብረው ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጉብኝቱ በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለው ደካማ የንግድ ስምምነት የሚፈተንበት ቁልፍ ወቅት ይሆናል።

ትራምፕ በባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ወዳጅም ሆነ ጠላት ሳይሉ በሁሉም የዓለም ሀገራት ላይ ከፍተኛ የማስመጫ ታክስ መጣላቸው ይታወሳል።

የዚህ ፖሊሲ ዋነኛ ውጤት በአሜሪካ እና በቻይና መካከል የተካሄደውና እርስ በእርስ እስከ 100 በመቶ የሚደርስ ታሪፍ እንዲጣጣሉ ያደረገው የንግድ ጦርነት ነበር። ታሪፉ ለጊዜው የቆመው ትራምፕ እና ሺ ባለፈው ጥቅምት ወር በደቡብ ኮሪያ ፊት ለፊት ከተገናኙ በኋላ ቢሆንም፣ ከሁለቱም ወገኖች የሚሰነዘሩ ዛቻዎች ግን አሁንም ቀጥለዋል።

ግንቦት 03/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *