የኢራን ጦርነት በዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ላይ የ25 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ አስከተለ

የአሜሪካና እስራኤል ከኢራን ጋር የጀመሩት ጦርነት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ኩባንያዎች ላይ ቢያንስ የ25 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ያደረሰ ሲሆን ሮይተርስ እኔደዘገበዉ ከሆነ ይህ የወጪ መጠን አሁንም እየጨመረ ነው ብሎል።

በዩናይትድ ስቴትስ፣ በአውሮፓ እና በኤዥያ የሚገኙ የኩባንያዎች መግለጫዎች እንደሚያመለክቱት፣ የንግድ ተቋማት በከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ንረት፣ በተበላሹ የአቅርቦት ሰንሰለቶች እና ኢራን በሆርሙዝ ስትሬት ላይ በፈጠረችው እገዳ ምክንያት ከባድ ፈተና ገጥሟቸዋል።

ቢያንስ 279 ኩባንያዎች የገጠማቸውን የፋይናንስ ኪሳራ ለመቀነስ የዋጋ ጭማሪ እና የምርት ቅነሳን ጨምሮ የተለያዩ መከላከያ እርምጃዎችን መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።

ይህ ቀውስ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ከሩሲያ-ዩክሬን ወረራ በመቀጠል የተከሰተ በመሆኑ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዓለም ንግድ ላይ ያለውን ስጋት ይበልጥ አሳድጎታል።

የዊርልፑል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ቢትዘር እንዳሉት፣ ይህ የኢንዱስትሪ ውድቀት ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ቀውስ ጋር ተመሳሳይ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል ።

ሳራ ዮሀንስ

ግንቦት 10/2018 ዓ›ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *