የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአገሪቱን የማምረት አቅም ለማሳደግና የንግድ ስርዓቱን ለማቀላጠፍ ባለፉት 10 ወራት 3መቶ29 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚገመት የቀረጥ ነፃ መብት ማበረታቻ መስጠቱን ገልጿል።
ይህ ማበረታቻ የተሰጠው በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣በማዕድን፣በቱሪዝም እና በመሰረተ ልማት ዘርፎች ለተሰማሩ ባለሀብቶችና የልማት ድርጅቶች ነው።
በተለይም በመንግስት እየተከናወኑ ለሚገኙ እንደ ኮሪደር ልማት ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች፣ ለግብርና ግብዓቶችና ለኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች የሚሰጠው የቀረጥ ነፃ መብት አገራዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተጠቅሷል።
ይሁን እንጂ ይህንን መብት ያለአግባብ ለመጠቀም በሞከሩ አካላት ላይ በተደረገ ጥብቅ ቁጥጥር 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የሚገመት ሀብት ወደ ገቢ እንዲመለስ መደረጉም ተገልጿል።
ኮሚሽኑ ማበረታቻው ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ለማረጋገጥ የቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ግንቦት 11/2018 ዓ.ም
