የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት በኢራን የጦርነት ስልጣን ላይ ሊደረግ የነበረው ድምፅ አሰጣጥ በድንገት ተሰረዘ

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የሪፐብሊካን መሪዎች፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኮንግረሱ ፈቃድ ውጭ በኢራን ላይ ጦርነት እንዳይከፍቱ የሚገድበውን የውሳኔ ሃሳብ ድምፅ የመስጠት ሂደት ሳይታሰብ ሰርዘዋል።

ይህ ውሳኔ የተሰረዘው፣ ተመሳሳይ ይዘት ያለውና የፕሬዝዳንቱን የጦርነት ስልጣን የሚገታ የሕግ ረቂቅ በአሜሪካ ሴኔት በኩል በከፍተኛ ድምፅ አልፎ ከጸደቀ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።

የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ (ኮንግረስ) ግልጽ የሆነ ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር፣ ከኢራን ጋር ወደ ሚደረግ ማንኛውም ወታደራዊ ግጭት እንዳይገቡ ለማገድ ያለመ ነበር።

የሪፐብሊካን መሪዎች ድምፅ የመስጠት ሂደቱን ለምን በድንገት እንደሰረዙት እስካሁን በግልጽ የሰጡት ማብራሪያ የለም።

ይሁን እንጂ ጉዳዩ በዋይት ሃውስ እና በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ መካከል በውጭ ጉዳይ ፖሊሲና በጦርነት አዋጅ ስልጣን ዙሪያ ያለውን ከፍተኛ ፍጥጫ የሚያሳይ መሆኑ ተነግሯል ዘገባው የአል አረቢያ ነው ።

ልዑል ወልዴ

ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *