የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1447ኛው የዒድ አለ-አድሃ (ዓረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
የምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በተለያየ ምክንያት በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን በመደገፍ ማክበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
“ኢትዮጵያውያን ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ የመረዳዳት እሴቶች አሉን” ያሉ ሲሆን በዓሉን በመተዛዘን፣ በመከባበር እና በመረዳዳት እንዲያከብረው ጥሪ በማቅረብ ለሀገር ሰላም እና አንድነት ሁሉም ዘብ ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።
እስልምና የሰላም እና የፍትሕ ሃይማኖት መሆኑን ገልጸው፣ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት እንዲሳተፉ እና ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለመደ በጎ ሚናውን እንዲጫወት ለሕዝበ ሙስሊሙ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል ።
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም
