ኢራን ለአሜሪካ ጥቃት አጸፋ ለመመለስ በባህሬን ኩዌት እና ጆርዳን ላይ ጥቃት ሰነዘረች

አሜሪካ የአንድ ሄሊኮፕተር መውደቅን ተከትሎ በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ በሚገኙ የኢራን ወደቦች ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ፣ የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኃይል በባህሬን፣ ኩዌት እና ጆርዳን በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የድሮንና የረጅም ርቀት ሚሳይል የአጸፋ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።

ኢራን በአጠቃላይ 21 የአሜሪካ ኢላማዎችን ማጥቃቷንና በጆርዳን የሚገኝ የF-35 ተዋጊ ጀት ማቆሚያን ጨምሮ አራቱን ማውደሟን እንዲሁም አንድ የአሜሪካ ድሮን መትታ መጣሏን የገለጸች ሲሆን፣ ከአሜሪካ ወገን ግን እስካሁን የተሰጠ ፈጣን አስተያየት የለም።

ይህንን ጥቃት ተከትሎ በባህሬን እና ኩዌት የአየር ጥቃት ሳይረን የተሰማ ሲሆን፣ የጆርዳን ጦር ደግሞ ከኢራን የተተኮሱ አምስት ሚሳይሎችን ያለ ምንም ጉዳት መትቶ ማክሸፉን አስታውቋል።

የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት የኢራን ፈጣን ምላሽ አሜሪካ ያለምንም ቅጣት ጥቃት እንዳትሰነዝር ለመግታት የታለመ አዲስ መመሪያን የሚያሳይ ቢሆንም፣ በተደጋጋሚ ክስተቶች ምክንያት በሁለቱም ወገኖች መካከል ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለው እምነት እየቀነሰ መጥቷል ብለዋል።

ይህ አዲስ የጥቃት ዙር የዓለምን ኢኮኖሚ ካናጋውና የነዳጅ እንዲሁም የምግብ ዋጋን ካናረው የኢራንና እስራኤል ከባድ የተኩስ ልውውጥ ማግስት የተከሰተ ሲሆን፣ የእስራኤል በሊባኖስ በሄዝቦላህ ላይ የምታካሂደው ዘመቻ ደግሞ የሰላም ሂደቱን ይበልጥ አዝጋሚ አድርጎታል።

ምንም እንኳን የቅርብ ጊዜ ጥቃቶች ቢኖሩም ሁለቱም ወገኖች ወደ ሙሉ ጦርነት መመለስ አይፈልጉም፤ ነገር ግን ወደ ድርድር ለመመለስ ያላቸው ፍላጎት በአሜሪካ ላይ ባላቸው እምነት ማነስ ምክንያት ተገቷል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ሳራ ዮሐንስ

ሰኔ 04/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *