ሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የነበሩ 1655 ኢትዮጲያዊያን ምህረት ተደረገላቸው አለ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር

ሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ እንዲሰጣቸው መደረጎ ተነግሯል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪያድ የሚገኘውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን እና ጂዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤት በማስተባበር ባደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1655 ዜጎቻችን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ እንዲሰጣቸው ተደርጓል።

ይህ ውጤት መንግሥት በውጭ ግንኙነቱ ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት የተገኘ ነው።
ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አኳያ በሳዑዲ አረቢያ ቀሪ የዲፕሎማሲ ጥረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተም ክትትል እያደረገ ነው።

በዚሁ አጋጣሚ መንግሥት ሕብረተሰቡ ከሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የታጀበ ሀሰተኛ ማታለያ ድርጊት የውጭ አገር ጉዞ ራሱን እንዲጠብቅ እያሳሰበ፤ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብሏል በማህበራዊ ትስስር ገጹ።

ሰኔ 04/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *