በስታቲስቲክስ ተግባር የተሰበሰበ የግለሰብ መረጃ በማንኛውም ተቋማት ዘንድ ለምርመራ ለደህንነት ለህግ ወይም ለአስተዳደራዊ ዉሳኔዎች እንዳይዉል ረቂቅ አዋጅ ይከለክላል ተብሏል ።
ይህ ረቂቅ አዋጅ ግንቦት 18 በተካሄደው 55ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ይታወሳል።
የዜጎች የግል መረጃ ምስጢራዊነት አጠባበቅን በተመለከተም በስታቲስቲክስ ተግባር የተገኘ የግለሰብ ዳታ ለስታቲስቲክስ ዓላማ ብቻ የሚያገለግል ነዉ ተብሏል።
በማንኛውም ሀገራዊ ወይም የዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ ለምርመራ፣ ለደህንነት፣ ለሕግ ወይም ለአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሊውል እንደማይችል ረቂቁ አሳስቧል።
የግለሰቦችን ማንነት የሚገልጽ መረጃ አሳልፎ መስጠት በረቂቁ መሰረት በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑ ተመላክቷል።
ረቂቅ አዋጁ በመረጃ አሰባሰብ ሂደት ላይ ለሚታዩ መሰናክሎች የቅጣት ድንጋጌዎችን አስቀምጧል።
ማንኛውም መረጃ እንዲሰጥ የተጠየቀ አካል የተሳሳተ መረጃ ቢሰጥ ወይም ለመተባበር ፈቃደኛ ባይሆን በወንጀል ሕግ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል ነዉ የተባለው።
ሊዲያ ደሳለኝ
ሰኔ 08/2018 ዓ.ም
