የአሜሪካ-ኢራን ስምምነትን 17 ሀገራት የተቀበሉት ሲሆን ሁሉም የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደገና እንዲከፈት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በእንግሊዝ ፣ በፈረንሣይ ፣ በጀርመን እና በጣሊያን የተሰጠዉ የጋራ መግለጫ ‹‹ይህ የክልሉን መረጋጋት ወደነበረበት ለመመለስ እና የዓለምን ኢኮኖሚ ለማረጋጋት የዕድል ጊዜ ነው›› ብለዋል።
ከመግለጫው በኋላም በሌሎች 13 አገሮች ስምምነቱ ተፈርሟል።
መሪዎቹ ዝርዝር ድርድሮች እንዲጠናቀቁ እና ስምምነቱ ‹‹በፍጥነት እና ሁሉን አቀፍ›› በሆነ መልኩ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
የሆርሙዝ ወሽመጥ በአስቸኳይ እንዲከፈት እና ‹‹ያለ ቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የመርከብ ነጻነት›› እንዲመለስ ጠይቀዋል።
ሌሎች የመግለጫው ፈራሚዎች ጃፓን፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ቤልጂየም፣ ቡልጋሪያ፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ኢስቶኒያ፣ ፊንላንድ፣ ግሪክ፣ ላቲቪያ፣ ፖላንድ እና ፖርቱጋል ናቸው።
ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በኢራን ላይ የአየር ጥቃት ከከፈቱ በኋላ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት ሲያለፍ በየካቲት ወር መጨረሻ በአካባቢ ውጥረቱ ተባብሶ ነበር፡፡
ቴህራን በባህረ ሰላጤው ሀገራት እና በእስራኤል ላይ ጥቃት በመሰንዘር እንዲሁም በሆርሙዝ ባህር ማለፍ ላይ እገዳ ጥላለች።
ዋሽንግተን እና ቴህራን ግጭቱን ለማስቆም የሚያስችለዉን ስምምነት ይፋ ከማድረጋቸዉ በፊት ሚያዝያ 8 በፓኪስታን አሸማጋይነት ጊዜያዊ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ስምምነቱ ሀምሌ 19 በስዊዘርላንድ በይፋ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ሰኔ 09/2018 ዓ.ም
