በ13,000 ዶላር የሚሸጠውና ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀሰው ዘመናዊ የሮቦት መጸዳጃ ቤት

​የቻይናው ዩባን ኩባንያ፣ መሰናክሎችን በመገንዘብ መጓዝና ራሱን ማፅዳት የሚችል ሺያኦባን የተሰኘ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚመራ የሮቦት መጸዳጃ ቤት ይፋ አድርጓል።

ይህ ቴክኖሎጂ ወደ መጸዳጃ ቤት መሄድ የሚለውን የሰው ልጅ ልማድ በመቀየር መጸዳጃ ቤቱ ራሱ ወደ ተጠቃሚው ዘንድ እንዲመጣ እያደረገ ይገኛል።

​በሻንጋይ የሕክምና ኤክስፖ ላይ የቀረበው ይህ ሮቦት በዋናነት የአካል ጉዳት፣ ከፊል አካል ጉዳት ወይም የመንቀሳቀስ ችግር ላለባቸው ወገኖች ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

መጸዳጃ ቤቱ የ”AI 3D”ዕይታ ሥርዓትን በመጠቀም መሰናክሎችን እያሸሸ እስከ አልጋ አጠገብ ድረስ መጓዝ ይችላል።

አገልግሎት ሰጥቶ ሲያበቃም የላይዳር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ራሱን ችሎ ቆሻሻ ወደሚያወርድበት ማቆሚያ ቦታ ተመልሶ የተጠራቀመውን ቆሻሻ ያስወግዳል።

ቆሻሻውን ካስወገደ በኋላም በከፍተኛ ግፊት በሚረጭ ውሃ እና በአልትራቫዮሌት (UV) ጨረር አማካኝነት ራሱን በራሱ እንደሚያነፃ ተገልጿል ።

​ይህ «ሺያኦባን» የተሰኘው የሮቦት መጸዳጃ ቤት በአሁኑ ወቅት በቻይና ገበያ በ13,000 ዶላር ገደማ እየተሸጠ ይገኛል።

ምርቱ ከቻይና ውጪ ስለመቅረቡ እስካሁን የተገለጸ ነገር ባይኖርም፣ የወደፊቱን የዕለት ተዕለት ሕይወትና የቴክኖሎጂ ዕድገት ደረጃ ግን በግልጽ አመላካች ሆኗል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

ሐመረ ፍሬው

ሰኔ 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *