የሌበር ፓርቲ አመራርን ለመተካት ውድድር ሊካሄድ ይችላል የሚል ግምት እየተጠናከረ ነው

ከጠቅላይ ሚኒስትርነት መልቀቃቸውን ካሳወቁት ኬር ስታርመር በኋላ አዲሱ የሜከር ፊልድ ፓርላማ አባል አንዲ በርንሃም የፓርቲውን መሪነት እና የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለመረከብ ቀዳሚ እጩ ተደርገው ይታያሉ።

ሆኖም የፓርቲው ፓርላማ አባላት ቻርንስ እና ዳሬን ጆንስ በአመራርነት ውድድሩ ለመሳተፍ እያሰቡ መሆናቸው ተዘግቧል።

ይህም በርንሃም ያለ ተቀናቃኝ ወደ ስልጣን እንዳይመጡ ለማድረግ የተጀመረ እንቅስቃሴ ነዉ ተብሎ እየታየ ነው፡፡

በተለይም የዳረን ጆንስ እጩነት ዕድሉ ዝቅተኛ ቢባልም እስካሁን ከውድድሩ ራሳቸውን አላገለሉም ተብሏል።

የቢቢሲ የፖለቲካ ተንታኝ ሄነሪ ዘፍማን እንደገለጹት፤ ሁለቱም እጩዎች ከሌበር ፓርቲ ፓርላማ አባላት በቂ ድጋፍ የማግኘታቸው ዕድል በአሁኑ ጊዜ ዝቅተኛ ቢመስልም የእጩነት ምዝገባ እስከሚከፈትበት ሀምሌ 9 ድረስ ሁኔታው ሊቀየር ይችላል።

በሌላ በኩል የቀድሞው የጤና ሚኒስትር ዌስ ስትሬቲንግ ለበርንሃም ድጋፋቸውን መግለጻቸው የእርሳቸውን እጩነት ይበልጥ አጠናክሮታል።

ትዕግስት ግርማ

ሰኔ 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *