የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ ጁንታ ፓሪስ “ከአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም በተቃራኒ እየተንቀሳቀሰች ነው” ሲል ከፈረንሳይ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጧል።
በፈረንሳይ እና በቀድሞ ቅኝ ግዛቷ ቡርኪና ፋሶ መካከል ያለው ግንኙነት ኢብራሂም ትራኦሬ እ.ኤ.አ. በ2022 በፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዙ እና ባብዛኛው ፀረ-ምዕራባውያን ፖሊሲዎችን መከተል ከጀመሩ በኋላ ይበልጥ እየተበላሸ መጥቷል።
የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ፒንግድዌንዴ ጊልበርት ኡዌድራኦጎ አርብ ዕለት በቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ፤ ፈረንሳይ በአገራቸው ላይ “ያልተቋረጠ የጣልቃ ገብነት እንቅስቃሴ” በማድረግ ጥፋተኛ መሆኗንና “የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም (የአዲሱ ቅኝ ግዛት) ምኞት” እንዳላት ከሰዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ውሳኔውን “የጠላትነት እና መሠረተ ቢስ” ሲል የጠራው ሲሆን፣ እርምጃው “የቡርኪና ፋሶ መንግሥት ያለበትን አሳሳቢ የውድቀት ጉዞ የሚያሳይ ነው” ብሏል።
በተጨማሪም ፈረንሳይ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቿ “ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ” አሳስባለች።
ቡርኪና ፋሶ ልክ እንደ ጎረቤቷ ማሊ ሁሉ፣ በግዛቱ ውስጥ ከተሰማሩት የፈረንሳይ ጦር ኃይሎች ጋር በመሆን ከዐሥር ዓመታት በላይ እስላማዊ አማፂያንን ስትዋጋ ቆይታለች።
ሰኔ 22/2018 ዓ.ም
ቡርኪና ፋሶ ከፈረንሳይ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች
