የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ እንዲሆን ተወሰነ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በ2018 የትምህርት ዘመን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ ከፍተኛ ዉጤት መመዝገቡን ጠቅሰው የተመዘገበው ውጤት አበራታች መሆኑን ተናግረዋል።
ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በ2018 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ በተማሪዎች ውጤት መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ ባደረገው ትኩረት ውጤቱ መመዝገቡን ተናግረው፤ፈተናውን በአጭር ጊዜ በማረም ውጤቱ ይፋ እንዲሆን ቀን ከሌት ሲሰሩ ለቆዩ የፈተና ክፍል ባለሙያዎችና ሂደቱን ሲደግፉ ለነበሩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው፤በከተማ አስተዳደሩ በ2018 ዓ.ም 85 ሺህ7መቶ37 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡
ሰኔ 22/2018 ዓ.ም
