አፍሪካ  በዓለም ንግድ ላይ ያላት ድርሻ 3 በመቶ መሆኑ ተገለፀ

አፍሪካ በዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ውስጥ ከሦስት አሥርተ ዓመታት በላይ ብትቆይም፣ አሁንም በዓለም ንግድ ያላት ድርሻ 3 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ቁጥር ደግሞ እንደ ቡና እና ማዕድናት ያሉ ጥሬ ዕቃዎች ሲወጡ፣ የአህጉሪቱ የንግድ ተሳትፎ ከዚሁ ከሦስት በመቶም በእጅጉ ዝቅ የሚል መሆኑ ነው የተጠቆመው።

ይህንን ዝቅተኛ ተሳትፎ ለመቀየርና አህጉሪቱን የንግድ ተጠቃሚ ለማድረግ፣ 22ኛው የአፍሪካ ከፍተኛ የንግድ ባለሥልጣናት ስብሰባ በናይጄሪያ አቡጃ መካሄድ ጀምሯል።

ባለሥልጣናቱ ለሦስት ቀናት በሚቆየው የሥራ ቆይታቸው፣ የቀረቡ የቴክኒክ ምክረ-ሃሳቦችን መርምረው ወደ ውሳኔ በመቀየር ለንግድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀርባሉ ተብሏል።

የዚህ ስብሰባ ዋነኛ ግብ አፍሪካ ጥሬ ዕቃዎችን ብቻ ከመላክ ባለፈ፣ እሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች ለዓለም ገበያ በማቅረብ ያላትን ድርሻ የምታሳድግበትን ስትራቴጂ መንደፍ እንደሆነ ተገልጿል።

ልዑል ወልዴ

ሰኔ 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *