ታዋቂው የቻይና ባለሀብት በአሜሪካ በ30 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

በአንድ ወቅት ከቻይና እጅግ ባለጸጋ ነጋዴዎች አንዱ እንደነበረ የሚነገርለት ጉዎ ዌንጉዊ በቢሊየን ዶላር በሚቆጠር የማጭበርበር ወንጀል በአሜሪካ ፍርድ ቤት የ30 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል።

የቀድሞው የሪል እስቴት ባለሀብት በ2017 ከቻይና በመሰደድ ወደ አሜሪካ ያቀና ሲሆን፤እዚያም እራሱን የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ተቺ አድርጎ በመቅረጽ በርካታ የኢንተርኔት ተከታዮችን ማፍራት ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ ጉዎ ሲንቀሳቀስ በነበረበት ወቅት በማደራጀት፣ በማጭበርበር እና ህገ-ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አድርጎ የማቅረብ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

የኒውዮርክ ፍርድ ቤት ዳኛ አና ሊሳ ቶሬስ በሰጡት ውሳኔ፤ ጉዎ ‹‹በቻይና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የሚፈልጉ ሰዎችን እምነት በመበዝበዝ›› የሰበሰበውን ገንዘብ ለራሱ ቅንጡ ህይወት ማደላደያ ማዋሉን ገልጸዋል።

የአሜሪካው አቃቤ ህግ ሾን ኤስ ባክሌይ ለቢቢሲ በሰጡት መግለጫ፤ ‹‹ጉዎ ከተሰጡት በርካታ ህጋዊ እድሎች ጋር ከመስማማት ይልቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የጣሉበትን እምነት ለግል ስግብግብነቱ ተጠቅሞበታል›› ብለዋል።

አቃቤ ህጉ አክለውም፤‹‹የዛሬው ውሳኔ ዝና እና ሀብት ከህግ በላይ ሊያደርጉ እንደማይችሉ እና ቤተሰቦችን በመበዝበዝ እራሳቸውን የሚያበለጽጉ አጭበርባሪዎች ከባድ መዘዝ እንደሚጠብቃቸው ያሳየ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል።

ሀና ሰይፉ

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *