ኦማን በሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤ በባሕር ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉ ፈንጂዎችን የማጽዳት ዋና ኃላፊነት በዋናነት በኢራን ላይ እንደሚወድቅ አስታዉቃለች።
ይህ መግለጫ የመጣው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ከኦማን ጋር በመተባበር የሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤን ከፈንጂ ለማጽዳት ዝግጁ መሆናቸውን ከገለጹ በኋላ ኢራን በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ባሰማችበት ወቅት ነው።
የኦማን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር ቢን ሐመድ አልቡሳይዲ ለፈረንሳዩ ሞንቴ ካርሎ ዱዋሊያ ሬዲዮ በሰጡት ቃል፤በአሜሪካና ኢራን መካከል በተደረሰው የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤና በዓለም አቀፍ እውቅና ባላቸው የመርከብ መጓጓዣ መስመሮች የፈንጅ አደጋ እንዳይኖር ማረጋገጥ በዋናነት የኢራን ኃላፊነት ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ በተጨማሪም ኦማን ጥያቄ በሚቀርብላት ጊዜ ለክልላዊና ለዓለም አቀፍ ጥረቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ትዕግስት ግርማ
ሰኔ 23/2018 ዓ.ም
