በቬንዙዌላ የተከሰተውን አስከፊ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ የመንግስት ምላሽ መዘግየትና ቸልተኝነት ህዝቡን ለከፍተኛ ቁጣና ቅሬታ ዳርጓል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
እስካሁን በደረሰው አደጋ ቢያንስ 1ሺህ7መቶ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ባለስልጣናት የገለጹ ሲሆን፤ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ ክስተቱን በሀገሪቱ ታሪክ ‹‹እጅግ አስከፊው የተፈጥሮ አደጋ››ሲሉ ጠርተውታል።
ሆኖም በፈራረሱ የሪል ስቴት እና የመኖሪያ ህንፃዎች ፍርስራሽ ስር የተረፉ ሰዎችን ለመታደግ የሚደረገው ጥረት እጅግ አዝጋሚ መሆን ነዋሪዎችን እያስቆጣ ይገኛል።
የመንግስት እርዳታ እና የማዳኛ ማሽነሪዎች በፍጥነት አለመድረሳቸውን ተከትሎ በቤሎ ሆሪዞንቴ እና መሰል መንደሮች የሚገኙ ነዋሪዎች የራሳቸውን ደህንነት ለአደጋ አጋልጠው በባዶ እጃቸውና በዶማ ፍርስራሹን እየቆፈሩ ሰዎችን ለማዳን ተገድደዋል።
ምንም እንኳን ከኮሎምቢያ፣ ኤል ሳልቫዶር እና አሜሪካ የመጡ የነፍስ አድን ቡድኖች ድጋፍ እያደረጉ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች የፍለጋ ስራው በይፋ መቋረጡ ተገልጿል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም በፍርስራሹ ስር ተቀብረው በመቅረታቸው የአደጋው እውነተኛ የጉዳት መጠን ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አክሏል።
እድላዊት ብርሃኑ
ሰኔ 23/2018 ዓ.ም
