ሩዋንዳ ዕድሜያቸው 60 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ዜጎች ልዩ የአረጋውያን የሕክምና አገልግሎት ጀመረች

የጤና ሚኒስትሩ ሳቢን ንሳንዚማና በፓርላማ የጋራ ስብሰባ ላይ እንዳወጁት፣ ይህ ልዩ የአገልግሎት ዓይነት የተጀመረው በሀገሪቱ የሰው ልጅ የዕድሜ ጣሪያ በመጨመሩ እና የአረጋውያን ቁጥር እያደገ በመምጣቱ ነው።

​እ.አ.አ በ2030 የዕድሜ ጣሪያ 80 ዓመት ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም የአረጋውያን ዜጎችን ቁጥር ይጨምረዋል ተብሏል።

አዲሱ የአረጋውያን ሕክምና አገልግሎት እንደ ሕፃናት ሕክምና ሁሉ ለአረጋውያን ፍላጎት ተስማሚ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑም ተነግሩለታል፡፡

ሩዋንዳ በአረጋውያን እንክብካቤ ላይ የሰለጠኑ ዶክተሮችን አስቀድማ ያዘጋጀች ሲሆን፣ እነዚህም አገልግሎት መስጠትና ተጨማሪ የጤና ባለሙያዎችን ማሰልጠን ይጀምራሉ።

​“ዋናው ነገር ዕድሜ ቁጥር ብቻ እንዲሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ጤናን መንከባከብ ነው። አንድ ሰው 80 ዓመት ደርሶ፣ የልጅ ልጆቹን አዝሎ፣ አሁንም ከእነሱ ጋር እግር ኳስ መጫወት መቻል አለበት” ብለዋል ንሳንዚማና።

ሐምሌ 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *