አሜሪካ በኢራን ላይ የድሮን ጀልባ ጥቃት ሰነዘረች።


ዩናይትድ ስቴትስ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው አልባ የድሮን ጀልባዎችን በመጠቀም በኢራን መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ፣ በቡሸር፣ ባንዳር አባስ፣ ኪሽ እና ቀሽም ደሴቶች ላይ ከፍተኛ ፍንዳታዎች ተከስተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ወደቦች ላይ የባህር ላይ ከበባ እንደሚጣልና ዋሽንግተን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ የ20 በመቶ ክፍያ እንደምትጠይቅ አስታውቀዋል።

​ኢራን በበኩሏ በኩዌት፣ ባህሬን እና ዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የአጸፋ ጥቃት መፈጸሟን ገልጻለች።

በተጨማሪም በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በሁለት የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ በሰነዘረችው የክሩዝ ሚሳኤል ጥቃት የአንድ ህንዳዊ ሰራተኛ ህይወት ማለፉ ታውቋል።

ይህንን ቀጠናዊ አለመረጋጋት ተከትሎ፣ የእስራኤል የደህንነት ኃይሎች በደቡባዊ ኬብሮን ሰፊ ወረራ በማድረግ በደርዘን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንን በቁጥጥር ስር አውለው የመስክ ምርመራ እያደረጉባቸው መሆኑን የፍልስጤሙ ዋፋ የዜና ወኪል ዘግቧል።

እድላዊት ብርሀኑ

ሐምሌ 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *