የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢራን በሀገራቸው ላይ አዲስ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ ጠንካራ ምላሽ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።
በዲሞና በተካሄደ ጉባኤ ላይ ኔታንያሁ ሲናገሩ ‹‹ለኢራን መሪዎች የምነግራቸው ነገር ቢኖር ጥቃት ከሰነዘራችሁብን ነገሮች ሰላማዊ ሆነው ይቀጥላሉ ብላችሁ እንዳታስቡ ነው›› ብለዋል።
ኔታንያሁ አክለውም ‹‹አንድ አካል ጥቃት ሲሰነዝርብን እኛ ደግሞ ወሳኝ በሆነ ምት ምላሽ የማንሰጥበት ዘመን አብቅቷል›› ብለዋል።
ጥቃቱ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ከዋና አጋራቸው ከአሜሪካ ጋር በጋራ ከፈጸሙት ጥቃት የበለጠ ኃይለኛ እንደሚሆንም ገልጸዋል።
ከጽሕፈት ቤታቸው በወጣው ቪዲዮ መሠረት ኔታንያሁ ቀደም ሲል በኢራን ላይ የተፈጸሙትን ጥቃቶች በማጣቀስ ‹‹ድጋሚ ይከሰታል ብላችሁ አትጠብቁ›› ብለዋል።
ምክንያቱም ድጋሚ ተመሳሳይ ነገር አይሆንም፤ ቀደሞም ቢሆን በራሱ በቂ ኃይል ነበረው። ይህ ግን የተለየና እጅግ የላቀ ኃይል ያለው ክስተት ይሆናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ሀና ሰይፉ
ሐምሌ 08/2018 ዓ.ም
