ትዕዛዙ የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን ቡድን ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ፣ ፕሬስና መረጃ ክፍል ኃላፊ እና የአውሮፓ ኅብረት የፕሮግራም ኦፊሰርን የሚመለከት ነው።
መንግሥት እስካሁን ለውሳኔው ይፋዊ ምክንያት አልሰጠም።
ከትዕዛዙ ቀደም ብሎ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደርና የልዑካን ቡድን ኃላፊ ዳንኤል አሪስቲ ጋዝቴሉሜንዲ ሰኔ 14 ቀን በቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተጠርተው ነበር።
ካራሞኮ ዣን-ማሪ ትራኦሬ፤ የአውሮፓ ፓርላማ ሀገሪቱ ላይ ያስተላለፈውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውሳኔ ጠላታዊ እና የውስጣዊ ጉዳይ “ጣልቃ ገብነት” በማለት በግንኙነቱ ወቅት ገልጸውታል።
ቡርኪና ፋሶ በሰኔ ወር ከፈረንሳይ ጋር ሙሉ በሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ያቋረጠች ሲሆን የፈረንሳይ ዲፕሎማቶች በሐምሌ ወር መጀመሪያ ሀገሪቱን ለቀው ወጥተዋል።
ሐምሌ 08/2018 ዓ.ም
