ትራምፕ ኢራን ንግግሯን ካልቀጠለች በስተቀር ድልድዮችን እና የኃይል ማመንጫዎችን በቦምብ እንደሚፈነዱ ዛቱ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገሪቱ ወደ ድርድር ካልተመለሰች በሚቀጥለው ሳምንት የኢራንን ድልድዮች እና የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን እንደሚመታ ዝተዋል

ፕሬዝዳንቱ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በሰጡት አስታያየ ሁለቱ ሀገራት ለተከታታይ አራት ቀን የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ ነበር

ትራምፕ በሚቀጥለው ሳምንት ለ ኢራን በጣም መጥፎ ጊዜ እንደሚሆን እና ወደ ጠረጴዛው ቀርበው ካልተደራደሩ የኢራንን የኃይል ማመንጫዎችን በሙሉ እንደሚያሶግዱ ተናግረዋል

የዩናይትድ ስቴትስ ተደራዳሪዎች ማክሰኞ ማምሻውን ለኢራን አቻዎቻቸው ስምምነት ቢያደርጉ ይሻላል፣ ​​አለበለዚያ ምንም የሚቀር ነገር አይኖርም ብለዋል

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) በሆርሙዝ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ በደርዘን የሚቆጠሩ የኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ያሉት ሲሆን ዓላማውም ኢራን የንግድ መርከቦችን እና የሲቪል ሠራተኞችን የማስፈራራት አቅም የበለጠ ለማዳከም ነው

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቴህራን ሚሳኤሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በዮርዳኖስ፣ ኩዌት እና ባህሬን መተኮሷን የኢራን መንግስት ቴሌቪዥን IRIB ዘግቧል ሲል ቢቢሲ ገልጿል

የኩዌቲ አየር መከላከያዎች በአሁኑ ጊዜ የኢራንን እኩይ ጥቃት ተከትሎ በጠላት ድሮኖች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው ሲል የኩዌት ጦር ተናግሯል

የባህሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎች እና ነዋሪዎች ተረጋግተው በአቅራቢያው ወደሚገኝ አስተማማኝ ቦታ እንዲያመሩ አሳስቧል

በተጨማሪም ዩኤስ ኢራን በክልሉ በሚገኙ ሰባት የንግድ መርከቦች ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ሆን ብላ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ ነው ስትል የሴንትኮም አዛዥ እንደገለጸው በዚህም ወደ 12 የሚጠጉ ሲቪል መርከበኞች ተገድለዋል፣ ጠፍተዋል ወይም ቆስለዋል ብሉዋል

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ሰኞ ምሽት እንዳስታወቀው የኢራን ክራይዝ ሚሳኤሎች በሁለት ብሄራዊ ታንከሮች ላይ ኢላማ አድርገው አንድ የህንድ መርከበኛን የገደለ ሲሆን ስምንት ሰዎችንም አቁስለዋል

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጠባቂ ኮርፕስ (IRGC) በበኩሉ ለቴሌግራም በሰጠው መግለጫ ጥቃቱን አረጋግጧል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው ፡፡

ሰላማዊት ዲታ

ሐምሌ 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *