በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ”አሜሪካን ስፔስ” ማዕከል ተመረቀ

የአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የ”አሜሪካን ስፔስ” ማዕከል መረቁ።
 
ኤምባሲው ለጣቢያችን በላከው መግለጫ ማዕከሉ በኢትዮጵያ 7ኛው፣ በሀገሪቱ ደቡብ ክፍል ደግሞ የመጀመሪያው ነው።
 
ማዕከሉ ለሁሉም ክፍትና ነፃ ሲሆን፤ ኮምፒውተሮችን ለመጠቀም፣ የ3D ህትመት ልምምድ ለማድረግ፣ ለትምህርት ዕድሎች ለመዘጋጀትና በቴክኖሎጂ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠናዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል መድረክ ነው ተብሏል።
 
አምባሳደሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከክልሉና ከከተማው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በብሔራዊ የምክክር ሂደትና በኢኮኖሚ ዕድሎች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፤ ከ22 ሺህ በላይ ሰራተኞችን የያዘውን የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክም ጎብኝተዋል።
 
ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *