የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በ3ኛው ዙር የኮሪደር ፕሮጄክት ልማት አካል በሆነው ከ22 ጎላጉል አደባባይ አንስቶ እስከ ኤምባሲዉ መጋጠሚያ ድረስ ባለው መስመር ከ61 በላይ አሽከርካሪዎች ማስቆም የሚያስችል የፓርኪንግ ስፍራ ላይ የቀለም ቅብ ስራ መከናወኑን አስታዉቋል።
በከተማዋ የሚከናወኑ የፓርኪንግ ስፍራዎች የትራፊክ ፍሰቱ እና እቅስቃሴው ሰላማዊ ደህንነቱም የተጠበቀ እንዲሆን የራሱን ጉልህ ሚና ይጫዎታል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሰልጣን በከተማዋ በሚከናወኑ መደበኛ እና ደራሽ ፕሮጀክቶች፣ የኮሪደር ልማቶች እና ወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች ፣በመንገድ ቀለም ቅብ ስራ፣ በምልክትና ማመላከቻዎች ተከላ ተሳታፊ እንደሆነም አስታዉቋል።
መረጃው የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ነው።
ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም
