በርካታ ስደተኞች ከሞሮኮ ወደ ስፔን የተሻገሩበትን ክስተት ተከትሎ የአውሮፓ ኅብረት ድንበሮች እንዲጠናከሩ አሳሰበ

የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚደንት ኡርሱላ ቮን ዲር ሊይን የድንበሮች ደኅንነት ለማስከበር የትብብር እርምጃ እንዲወሰድ አሳሰቡ።

ፕሬዚደንቷ ይህን ያሉት ባለፈው ሳምንት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ከሞሮኮ ወደ ስፔን መሻገራቸውን ተከትሎ ነው።

አሁን ላይ ከተሻግረው የነበሩት 69 ሺህ 5መቶ ገደማ ስደተኞች ወደ ሞሮኮ መመለሳቸው ተገልጿል።

ስደተኞቹ በዋና እና በእግር የስፔን ግዛት ወደሆነችው ሲዩታ ለመግባት በሚሞክሩበት ጊዜ በስፔን በኩል 72 ሰዎች ሲሞቱ በሞሮኮ በኩል ደግሞ 11 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

የአውሮፓ ኅብረት የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮችም በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ዛሬ ማክሰኞ በቪዲዮ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳሉ።

አስቸኳይ ስብሰባው የተጠራው በሲዮታ የታየው ክስተት በተወሰኑ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ውጥረት ውስጥ ከከተተው በኋላ ነው።

በሲዩታ ያጋጠመውን የስደተኞች ጎርፍ ተከትሎ ጣልያን ከስፔን ጋር ያላትን እና ያለቪዛ በአገራቱ መካከል መንቀሳቀስ የሚያስችለውን ሸንገን ቪዛ በጊዜያዊነት አግዳለች።

የሸንገን ስምምነት ከ4መቶ50 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ 29 የአውሮፓ አገራት ያለድንበር ፍተሻ ወይም ያለቪዛ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ይፈቅዳል።

ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *