በደቡባዊ ሩሲያ በሰው በተጨናነቀ የባህር ዳርቻ ላይ በተሰነዘረ የድሮን ጥቃት የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ

​በደቡባዊ ሩሲያ ክራስኖዶር ክልል አርኪፖ-ኦሲፖቭካ መንደር አቅራቢያ በሚገኝ የባህር ዳርቻ ላይ ዩክሬን በሰነዘረችው የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት የሶስት ህጻናትን ህይወት ጨምሮ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የክልሉ ገዥ ቬኒያሚን ኮንድራቲዬቭ በጥቃቱ በአጠቃላይ 40 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና 17ቱ ለተሻለ ህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልጸው፣ ድርጊቱን “በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሆን ተብሎ የተሰነዘረ ጥቃት” ሲሉ ኮንነዉታል።

ዩክሬን በበኩሏ ስለጉዳዩ እስካሁን የሰጠችው ይፋዊ አስተያየት የለም።

​ከፍንዳታው በፊት ግን የተኩስ ድምፅ መስማታቸውን የአይን እማኞች የተናገሩ ሲሆን፣ የሩሲያ ሚዲያዎች ደግሞ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ስርአት ድሮኑን ለመምታት ያደረገው ሙከራ ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል።

​በሌላ በኩል ሩሲያ እ.ኤ.አ በየካቲት 2022 ዩክሬን ላይ ሙሉ በሙሉ ወረራ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በመኖሪያ አካባቢዎች እና በከተሞች ላይ ባደረሰችው ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

ሰላማዊት ዲታ

ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *