የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦችን የሚያጣጥም የ120 አባላት ስብስብ ማቋቋሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከስምንቱ የአጀንዳ ቡድኖች የተሰበሰቡ ምክረ ሃሳቦችን እርስ በእርስ የሚጋጩ ነገሮች እንዳይኖሯቸው የማጣጣም እና ድግግሞሾችን ወደ አንድ የማምጣት ሀላፊነት የተጣለበት የ120 አባላት ስብስብ ማቋቋሙን ገለጸ።
 
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ እንደተናገሩት፣ ይህ ስብስብ ኮሚሽኑ አጠቃሎ ለሚያቀርበው የምክረ ሃሳብ ሰነድ ወጥነት እንዲኖረው የሚያስችል ስራ ይሰራል።
 
ለእያንዳንዱ ስምንት አጀንዳ ቡድን 15 ያህል አባላት የተመረጡ ሲሆን፣ እስከ መጪው ሰኞ ድረስ የማጣጣም ስራቸውን አጠናቀው በጋራ ማረጋገጫ ስርዓት አልፎ ለ500 አባላት የውይይት ቡድን ለተጨማሪ አስተያየት እንደሚያቀርቡ ተገልጻል።
 
በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከታቀዱት ስራዎች መካከል ሶስት አራተኛ ያህሉን ማጠናቀቁንና ሁሉም ተመካካሪ ቡድኖች በቀረቡት ምክረ ሐሳቦች ላይ ተስማምተው መፈረማቸውን አስታውቋል።
 
ከሐምሌ 8 ቀን ጀምሮ ዋናውን ጉባኤ በመክፈት የተጀመረውና በስምንት አጀንዳዎች ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው የምክክር ሂደት፣ በዛሬው እለት 30ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን ኮሚሽኑ ሂደቱን በተቀመጠለት ጊዜ ሰሌዳ አጠናቅቃለሁ ብሏል።
 
ቁምነገር አየለ
 
 ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *