በፕሮግራሙ አምስት አንኳር ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ የተሰራ ሲሆን፣ ከ5 ሺህ በላይ የሰለጠኑ ባለሙያዎች የቤት ለቤት የምክር አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። በተጨማሪም ለትውልድ ግንባታ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉ 1 ሺህ 155 የህጻናት ማቆያዎች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
ድጋፍ ለሚሹ አያሌ እናቶችና ህጻናት ተከታታይ የአልሚ ምግብና የህክምና ክትትል ከመደረጉም በላይ፣ ህጻናቱ በጨዋታ መልክ ለመደበኛ ትምህርት ዝግጁ እንዲሆኑ ተደርጓል ብሏል ከተማ አስተዳደሩ።
ይህ ፕሮግራም ለወላጆች እፎይታን፣ ለህጻናት ደግሞ ብሩህ ተስፋን ማብሰራቸው በጥናት መረጋገጡ ተጠቅሷል።
ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወነው የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም 1.3 ሚሊዮን ገደማ ህጻናትን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ
