የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር በዩክሬን ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ

የቀድሞው የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ሚካይሎ ፌዶሮቭ የጦርነት ጊዜ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህም ሩሲያ ሙሉ በሙሉ ወረራ ካካሄደችበት ከሶስት ዓመታት ወዲህ በዜለንስኪ ፕሬዝዳንትነት ላይ የተደቀነ ትልቁ ፉክክር ተገርጎ ተወስዱዋል።

ፌዶሮቭ ባለፈው ማክሰኞ በዩቲዩብ ላይ ባሰራጩት መልእክት ‹‹ዲሞክራሲ በሩሲያ ታግቶ ሊያዝ አይገባም ›› ብለዋል አክለውም ዩክሬን እየተዋጋች ያለችው “በእርግጥም ነፃ የአውሮፓ ሀገር ሆና ለመቀጠል ስለምትፈልግ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

እ.ኤ.አ. በ2022 ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ዩክሬን በወታደራዊ አዋጅ ስር የምትገኝ ትገኛለች ይህም ማለት ምርጫዎች ታግደዋል ማለት ነው።

ፌዶሮቭ ከተሾሙ ከስድስት ወራት በኋላ ባለፈው ወር ሳይታሰብ ከመከላከያ ሚኒስትርነታቸው መባረራቸው የሚታወስ ሲሆን ፤ መባረራቸው በመላው በሀገሪቱ ተቃውሞዎችን ቀስቅሷል፡፡

ፌዶሮቭ የመከላከያ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት ሚኒስቴሩን በማንቃት፣ ሙስናን በመታገል እና መረጃዎችን በመጠቀም በግንባር ላይ ያለውን አፈፃፀም ለማሻሻል በመስራት ምስጋና ተቸሯቸዋል።

የእሳቸው ከኃላፊነት መነሳት እና በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አሌክሳንደር ሲርስኪ መካከል ከተፈጠረው ውጥረት ጋር የተያያ እንደሆነም ይታመናል።

ሀና ሰይፉ

ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *