በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር 9 የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገለጸ።

የትምህርት ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ብቁ፣ ተወዳዳሪና ሥነ-ምግባር ያላቸው የወደፊት መሪዎችን ለማፍራት የሚያግዙ ሲሆን፤ ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ በተግባርና በክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ይሰጣሉ።
 
የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራት ማሻሻል መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዮሐንስ ወጋሶ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ባለፉት 5 ዓመታት በትምህርት ዘርፉ ከተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
ባለፈው ዓመት ሥራ በጀመሩ 5 የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 1,250 የተሻለ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች የትምህርት እድሉ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ዶ/ር ዮሐንስ ገልጸዋል።
 
ከዚህም ሌላ ከቻይና መንግሥት ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት፣ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ የቻይንኛ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት መሰጠት እንደሚጀምር ተመላክቷል።
 
በአዲስና ቀደም ሲል በጀመሩት ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች የምዝገባ ሥራ በመስመር ላይ (በበይነ መረብ) እየተከናወነ ይገኛል።
 
ትምህርት ሚኒስቴር በመላ ሀገሪቱ 13 ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት በሰፊው እየሰራ መሆኑን ገልጾ፤ ወላጆችና ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች ከዚህ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።
 
ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *