ኢትዮጵያ በሙዝ ምርት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን የጥራት ደረጃን ማሻሻል እንዳለባት ተገለጸ

“በሙዝ እሴት ወደ ላቀ ስኬት” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማህበር (EHPEA) ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ ጉባኤ በሂልተን ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል::

በጉባዔው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ በሙዝ ዘርፍ ያላትን አቅም ወደ ካፒታል ለመለወጥ የጥራት ቁጥጥር ላይ በትኩረት መሥራት ይኖርባታል ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሙዝ ምርት አቅም ቢኖራትም፣ ምርቱን ወደ ዓለም ገበያ ለማውጣት የጥራት ደረጃና የጤና ጥበቃ መስፈርቶችን ማሟላት ዋነኛው ፈተና ሆኖ ቆይቷል።

እስካሁን ያለው የኤክስፖርት እንቅስቃሴ በጅቡቲና በሶማሊያ ገበያዎች ላይ ብቻ የተገደበ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ኢትዮጵያን በዓለም የሙዝ ላኪዎች ካርታ ላይ ለማስፈር ከምርት መጠን ባለፈ ለጥራት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ከልማዳዊ አሰራር ወደ ገበያ ተኮር ስርአት ለመቀየር በርካታ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማድረጉን የገለጹ ሲሆን፣ ላኪዎችና አምራቾች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበዋል።

አዲስዓለም አበበ

ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *